Wednesday, December 2, 2015

ቅርሱ የሚገኝበት የጉዳት ሁኔታ

ካለፈው የቀጠለ...................

የሰሜን አቅጣጫ ፊት ለፊቱ ግንብ (ዋናው መግቢያ)
·        በሰሜን ምስራቅ የሚገኘው ጠርዝ ቁልቁል በረጅም ተነስጥቋል
·        በሰሜን ምስራቅ ጠርዝ የሚገኘው በር የላይኛው ቀሰተ ደመና ግንብ ፈራርሷል
·        ከዋናው መግቢያ በር በስተግራ የሚገኘው በር የላይኛው ግንብ ሙሉ ለሙሉ ተሰንጥቋል
·        ከዋናው መግቢያ በር በስተግራ የሚገኘው ግንብ ከላይ ወደ ታች በግማሽ ተሰንጥቋል
·        የቅድስቱ የላይኛው የፈራረሰው ግድግዳ ክፍል በጭቃ ግንብ ተስርቷል
የምስራቅ አቅጣጫ ግንብ
·        በሰሜን መእራብ ጠርዝ የሚገኘው በር የላይኛው ቀስተ ደመና ግንብ ፈራርሷል
·        አራት የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተሰነጠቀ ቁልቁል ወደታች ሶስት ቦታ በመካከለኛ ደረጃ የተሰነጠቀ
·        የቅድስቱ የላይኛው የፈራረሰው ግድግዳ ክፍል በጭቃ ግንብ ተሰርቷል
የምስራቅ አቅጣጫ ግንብ
·        የሁለቱ በሮች በላይ የሚገኘው ግንብ ቁልቁል ሁለት ቦታ በመካከለኛ ደረጃ የተሰነጠቀ
·        በድንጋይና ጭቃ ከተገነባው (የተደፈነው) ግንብ ላይ የሚገኘው የኖራ ግንብ ቁልቁል ሶስት ቦታ በመካከለኛ ደረጃ የተሰነጠቀ
·        የውጪኛው የላይኛው የፈራረሰው ግድግዳ ክፍል በጭቃ ግንብ ተሰርቷል
የደቡብ አቅጣጫ ግንብ
·        በድንጋይና ጭቃ ከተገነባው (የተደፈነው) ግንብ ላይ የሚገኘው የኖራ ግንብ ቁልቁል ሶስት ቦታ በመካከለኛ ደረጃ የተሰነጠቀ
·        የሁለቱ በሮች በላይ የሚገኘው ግንብ ቁልቁል ሁለት ቦታ በመካከለኛ ደረጃ የተሰነጠቀ
በግቢው ውስጥ የሚገኘው ሙዚየም
·        የሙዚየሙ አራና ግድግዳ የሚጋጠሙበት ቦታ ወደ ውስጥ እያሰረገ ግንቡ እርጥብት ያዘለ መሆኑ
·        የጣራው ሁለት የውሃ ማስወገጃ አሸንዳዎች በአፈር ዘግቶት ተደፍነው ጣራው ላይ ውሃ እያዘለና በዲንጋዩቹ እየሰረገ የሕንጻውን ግንብ  ወለልና የኮርኒሱ ጣውላ እያረጠበ መሆኑ
·        አብዛኛው ውጫዊው ግድግዳ በቁጥቋጦዎቻ አረሞች ተሸፍኗል
ከዚህ በፊት የተደረጉ የጥገናና ግንባታ ስራዎች
·        አግባብ ያላቸው ቢሮዎችና መምሪያዎች ሳያውቁ የቅድስቱ ወለል በሲሚንቶ ከውስጥ ከተገረፈ በኋላ ከላይ ጅብስምና ቀለም የተቀባ መሆኑ
·        በምስራቅ አቅጣጫ የቅድስቱ ክፍት በሮች በመድፈን መስኮት ተስርቷል
·        የቤተክርስቲያኗ ጣራ በቆርቆሮ ተቀይሯል
·        በውጭ በኩል ዙሪያውን የሸክላ ምሶሶ በአዲስ መልክ ተገንብቷል
·        የቤተ መቅደሱ መግቢያ በግራ በኩል ለምጽዋት መሰብሰቢያ ግንቡን ስልሳ በስላ ሳ.ሜ ስፋት በመቆፍቆፍ ተገንብቷል
·        ወለሉ ዙሪያውን በሲሚንቶ ተሰርቷል፤ የወለሉ ከፍታም እንዲጨምር ተደርጓል
·        በጣሊያን ወረራ ወቅት የቤተክርስቲያኑን ካርታና ፕላን በ1931 ተሰርቷል
·        ከ1971 ኢንጂሊኒ በተባለ የዩኔስኮ መሃንዲስ ማስተር ፕላን ተሰርቷል
·        በ1996 የቤተክርስቲያኑ ዋና ግድግዳ ጣራውን መሸከም ባለመቻሉ ከውጭ የሸክላ ቢሞችን በመራት የቆርቆሮ ጣሪያ እንዲሸከመው ተደርጓል
·        የቤተክርስቲያኑ ቤተልሔም በአዲስ ተሰርቷል
·        አዳዲስ የመቃብር ቤት ሕንጻዎች ተገንብተዋል

ይቆየን......................................................