Wednesday, December 2, 2015

ቅርሱ የሚገኝበት የጉዳት ሁኔታ

ካለፈው የቀጠለ...................

የሰሜን አቅጣጫ ፊት ለፊቱ ግንብ (ዋናው መግቢያ)
·        በሰሜን ምስራቅ የሚገኘው ጠርዝ ቁልቁል በረጅም ተነስጥቋል
·        በሰሜን ምስራቅ ጠርዝ የሚገኘው በር የላይኛው ቀሰተ ደመና ግንብ ፈራርሷል
·        ከዋናው መግቢያ በር በስተግራ የሚገኘው በር የላይኛው ግንብ ሙሉ ለሙሉ ተሰንጥቋል
·        ከዋናው መግቢያ በር በስተግራ የሚገኘው ግንብ ከላይ ወደ ታች በግማሽ ተሰንጥቋል
·        የቅድስቱ የላይኛው የፈራረሰው ግድግዳ ክፍል በጭቃ ግንብ ተስርቷል
የምስራቅ አቅጣጫ ግንብ
·        በሰሜን መእራብ ጠርዝ የሚገኘው በር የላይኛው ቀስተ ደመና ግንብ ፈራርሷል
·        አራት የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተሰነጠቀ ቁልቁል ወደታች ሶስት ቦታ በመካከለኛ ደረጃ የተሰነጠቀ
·        የቅድስቱ የላይኛው የፈራረሰው ግድግዳ ክፍል በጭቃ ግንብ ተሰርቷል
የምስራቅ አቅጣጫ ግንብ
·        የሁለቱ በሮች በላይ የሚገኘው ግንብ ቁልቁል ሁለት ቦታ በመካከለኛ ደረጃ የተሰነጠቀ
·        በድንጋይና ጭቃ ከተገነባው (የተደፈነው) ግንብ ላይ የሚገኘው የኖራ ግንብ ቁልቁል ሶስት ቦታ በመካከለኛ ደረጃ የተሰነጠቀ
·        የውጪኛው የላይኛው የፈራረሰው ግድግዳ ክፍል በጭቃ ግንብ ተሰርቷል
የደቡብ አቅጣጫ ግንብ
·        በድንጋይና ጭቃ ከተገነባው (የተደፈነው) ግንብ ላይ የሚገኘው የኖራ ግንብ ቁልቁል ሶስት ቦታ በመካከለኛ ደረጃ የተሰነጠቀ
·        የሁለቱ በሮች በላይ የሚገኘው ግንብ ቁልቁል ሁለት ቦታ በመካከለኛ ደረጃ የተሰነጠቀ
በግቢው ውስጥ የሚገኘው ሙዚየም
·        የሙዚየሙ አራና ግድግዳ የሚጋጠሙበት ቦታ ወደ ውስጥ እያሰረገ ግንቡ እርጥብት ያዘለ መሆኑ
·        የጣራው ሁለት የውሃ ማስወገጃ አሸንዳዎች በአፈር ዘግቶት ተደፍነው ጣራው ላይ ውሃ እያዘለና በዲንጋዩቹ እየሰረገ የሕንጻውን ግንብ  ወለልና የኮርኒሱ ጣውላ እያረጠበ መሆኑ
·        አብዛኛው ውጫዊው ግድግዳ በቁጥቋጦዎቻ አረሞች ተሸፍኗል
ከዚህ በፊት የተደረጉ የጥገናና ግንባታ ስራዎች
·        አግባብ ያላቸው ቢሮዎችና መምሪያዎች ሳያውቁ የቅድስቱ ወለል በሲሚንቶ ከውስጥ ከተገረፈ በኋላ ከላይ ጅብስምና ቀለም የተቀባ መሆኑ
·        በምስራቅ አቅጣጫ የቅድስቱ ክፍት በሮች በመድፈን መስኮት ተስርቷል
·        የቤተክርስቲያኗ ጣራ በቆርቆሮ ተቀይሯል
·        በውጭ በኩል ዙሪያውን የሸክላ ምሶሶ በአዲስ መልክ ተገንብቷል
·        የቤተ መቅደሱ መግቢያ በግራ በኩል ለምጽዋት መሰብሰቢያ ግንቡን ስልሳ በስላ ሳ.ሜ ስፋት በመቆፍቆፍ ተገንብቷል
·        ወለሉ ዙሪያውን በሲሚንቶ ተሰርቷል፤ የወለሉ ከፍታም እንዲጨምር ተደርጓል
·        በጣሊያን ወረራ ወቅት የቤተክርስቲያኑን ካርታና ፕላን በ1931 ተሰርቷል
·        ከ1971 ኢንጂሊኒ በተባለ የዩኔስኮ መሃንዲስ ማስተር ፕላን ተሰርቷል
·        በ1996 የቤተክርስቲያኑ ዋና ግድግዳ ጣራውን መሸከም ባለመቻሉ ከውጭ የሸክላ ቢሞችን በመራት የቆርቆሮ ጣሪያ እንዲሸከመው ተደርጓል
·        የቤተክርስቲያኑ ቤተልሔም በአዲስ ተሰርቷል
·        አዳዲስ የመቃብር ቤት ሕንጻዎች ተገንብተዋል

ይቆየን......................................................

Friday, November 27, 2015

የአጣጣሚ ሚካኤል የጥገና ፕሮፖዛል


ጥቅምት 2008 ዓ.ም

ክፍል አንድ

የቤተክርስቲያኑ አሰራርና ነባራዊ ሁኔታ


የደብረ ገነት አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ንጉስ አድባር ሰገድ ዳዊት ተሰርቶ ተጠናቀቀ።  ንጉሰ ነገሥቱ በዘመኑ ከግብጽ አሌክሳንደርያ በመጡት የኢትዮጵያ ጳጳስ አቡነ ክርስቶደሉ ባላባቱና ም ዕመናኑ በተገኙበት ሰኔ 1 ቀን 1709 ተመረቀ።

በአራት ማዕዘን ቅርጽ የተሰራው ይህ ቤተክርስቲያን ግድግዳው በጥቁር ድንጋይና ተቃትሎ ከስድስት ወር እስከ ሁለት ዓመት በውሃ ተዘፍዝፎ በተብላላ ኖራ ተገብቷል።  በሮቹ ከቁስቋም ተጠርቦ በመጣ ቀይ ልዝብ ድንጋይ በቅስት ተጌጡ።  ጣራው በባኅላዊ

Thursday, November 26, 2015

ኑ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ እንስራ!!!!! ነህ 2:20


 ለነፍሳችን ቤዛ የሚሆንልንን መንፈሳዊ ስራ በመስራት የአቅማችንን በማድረግ የተጀመረውን ህንጻ ቤተክርስቲያን ከፍጻሜ እናድርስው፡፡ 

በመጀመርያ ይህን ሁሉ ላደረገ ልዑል እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው እንላለን!!

                                                              ለበረከት ተጠርታችኃል


አሁንም፥ እነሆ፥ እግዚአብሔር ለመቅደስ የሚሆን ቤትን ትሠራ ዘንድ መርጦሃልና ጠንክረህ ፈጽመው። (መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 28፡10)


ለዚህም የተቀደሰ አላማ እጃችሁን በመዘርጋት እንድትረዱና የበረከቱ ተካፋይች ትሆኑ ዘንድ ቅዱስ ሚካኤል   ስም እንጠይቃለን፡

ደብረ ገነት አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ጎንደር እድሳት


Thursday, November 19, 2015

የደብረ ገነት አጣጣሚ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የዕድሳት ፕላን


ትንቢተ ሐጌ 1፥8
ወደ ተራራው ውጡ፥ እንጨትንም አምጡ፥ ቤቱንም ሥሩ እኔም በእርሱ ደስ ይለኛል፥ እኔም እመሰገናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር፦